📍 Guangzhou
📅 July 1, 2026
✍️ ECC Communications
የኢትዮጵያ ቀን በጓንዡ በድምቀት ተከበረ
On 27th June, Ethiopian Day 2026 was celebrated in Guangzhou with diaspora members, embassy representatives, Ethiopian Airlines colleagues, Chinese government representatives, friends, and partners.
የኢትዮጵያ ቀን በቻይና የሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት፣ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ ባልደረቦች፣ ከቻይና የመንግስት ተወካዮች፣ ከኢትዮጵያ ወዳጆቻች እና አጋሮቻች ጋር በመሆን በጓንዡ በድምቀት ተከብሯል።
ከፕሮግራሙ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ አየር መንገድ 80ኛ ዓመት የምስረታ በአልም የተከበረ ሲሆን፣ የሀገራችን ባህል እና እሴት፣ አብሮነት እንዲሁም ዘመናዊነት በማጉላት በድምቀት ተከብሯል።
በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሚስዮን መሪ ክቡር አምባሳደር ተፈራ ደርበው ባስተላለፉት መልዕክት በቻይና የኢትዮጵያውያን ማህበር አመራሮች፣ ለትጉ በጎ ፈቃደኞች፣ እንዲሁም በአሉ እውን እንዲሆን ቁርጠኝነት፣ ብርቱ ጥረት ላሳዩና እና በትጋት ለሰሩ ለጓንዡ የዳያስፖራ ማህበረሰብ ምስጋና በማቅረብ፣ በዴሞክራሲያዊ ሂደት 7ተኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫን በተሳካ ሁኔታ ማከናወናችንን በማስታወስ ይህ ስኬት፤ ኢትዮጵያውያን በሰላማዊ ተሳትፎ፣ ገንቢ በሆነ ውይይት፣ እንዲሁም ለሀገራዊ ዕድገት ባላቸው የጋራ ቁርጠኝነት የራሳቸውን መጻኢ ዕድል ለመቅረጽ ያሳዩትን ጽኑ ፍላጎትና ስኬት የሚያንጸባርቅ መሆኑ፣ ዴሞክራሲ በአንድ ጀንበር የሚደረስበት መዳረሻ ሳይሆን፤ ትዕግስትን፣ ኃላፊነትን እና የጋራ ጥረትን የሚጠይቅ ቀጣይነት ያለው ጉዞ መሆኑ፣ ወደ ፊት ስንጓዝ ብዝኃነታችንን የጥንካሬያችን ምንጭ አድርገን እንድንቀበል ትብብርን እና አንድነትን ማስቀደም እንደሚገባን አደራ በማለት ዳያስፖራው በእውቀትና በሀብት ለአገር ልማት የበኩሉን በየዘርፉ እንዲያበረክት ጥሪ አስተላልፈዋል።
በበዓሉ የሀገራችን ባህላዊ ምግብ፣ የቡና አፈላል ስነ-ስርዓት፣ ሙዚቃ እዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ ዝግጀቶች የተደረጉ ሲሆን፣ የዳያስፖራ አመራሮች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተወካይና የቻይና የመንግስት ተወካዮች ንግግር አድርጎዋል። ዝግጅቱ ልዩ ልዩ የዳያስፖራውን ማህበራዊ ግንኙነትና ትስስር የሚያጠናክሩ የመዝናኛ ፕሮግራሞች፣ የባህል ፋሽን ሾውና የተለያዩ ውድድሮች እንዲሁም እውቅና የመስጠት ፕሮግራም በማከናወን ፍፃሜው አግኝቷል።